Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በድምቀት እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ የነበራቸውን አካላት አመስግነዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው፤ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለዋጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓልን ከመላው ኢትዮጵያውያን እና ዓለም ህዝቦች ጋር በዘመኑ ቴክኖሎጂ በያሉበት እጅግ ደስ በሚል ሁኔታ አክብረናል ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ፀጥታውን በመጠበቅ፣ ህዝቡን በማስተባበርና በማስተናገድ የበኩላቸውን ለተወጡ ሁሉ አቶ ደስታ ሌዳሞ ምስጋና አቅርበዋል።

እንግዶቻችን ከእኛ ጋር በማሳለፍ ለበዓሉ ስኬት አስተዋጽኦ ስለአበረከታችሁ በራሴና በሲዳማ ህዝብ ስም ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ትናንትና ዛሬ በድምቀት መከበሩ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.