Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የዲ ኤስ ቲቪ ስትሪም ጥቅል ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ከመልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዲ ኤስ ቲቪ ስትሪም ጥቅል የተባለ አገልግሎት ይፋ አድርጓል።

ስምምነቱ ቀልጣፋ ፈጣንና በየትኛውም ጊዜና ቦታ የላቀ ጥራት ያላቸውን ይዘቶች በተለያዩ ስማርት ስልኮች ማግኘት የሚያስችል ነው።

ጥቅሉ ከድምጽና ኢንተርኔት ግንኙነት በተጨማሪ የተለያዩ ተወዳጅ የስፖርት ቻናሎችን ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ማየት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ሀገርኛ ይዘቶችን፣ ዓለም አቀፍ ፊልሞችን፣ ዶክመንተሪዎችንና የተለያዩ ሾዎችን መመልከት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በወቅቱ እንዳሉት፤ ትብብሩ ኢትዮ ቴሌኮም ሁሉንም አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተጓዘበት ያለውን ርቀት የሚያሳይ ነው።

የመልቲ ቾይስ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ገሊላ ገብረሚካኤል በበኩላቸው ዲ ኤስ ቲቪ ስትሪም ጥቅል አገልግሎት ጎጆ ቤተሰብ፣ ሜዳ ፕላስና ፕሪሚየም አማራጮችን ያካተተ በመሆኑ ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት መርጠው እንዲጠቀሙ ያስችላል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.