3 ሺህ 539 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 539 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ ከተመለሱት መካከል 2 ሺህ 999 ወንዶች፣ 501 ሴቶች እና 39 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፤ 105 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራው ባለው ስራ እስካሁን 8 ሺህ 917 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።