በአሶሳ ከተማ የሶስት ክልሎች የሰላምና የልማት የጋራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኢፍጣር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የኦሮሚያ እና የጋምቤላ ክልሎች የጋራ የሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዘጋጅነት የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።
መርሐ ግብሩ የክልሎቹን ህዝብ ወንድማማችነት፣ አብሮነትና አንድነትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።
በክልሎቹ መካከል የተጀመረው የሰላምና የልማት ትብብር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርስ የገለጹት የሶስቱ ክልሎች የሰላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሮምሳ ሰለሞን ናቸው።
በመርሐ ግብሩ የታደሙ የሃይማኖት አባቶች ህዝበ ሙስሊሙም በረመዷን ወቅት ያሳየውን የመተባበር እና የመረዳዳት ባህል በሌሎች ጊዜያቶችም አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።