Fana: At a Speed of Life!

መጋቢት 24ን ምክንያት በማድረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል መጋቢት 24ን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡

መጋቢት 24 ሀገራዊ ለውጡ ዕውን የሆነበት እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበት ዕለትን ምክንያት በማድረግ ነው ስፖርታዊ እንቅስቃሴው እየተደረገ የሚገኘው።

በተጨማሪም ስፖርታዊ እንቅስቃሴው በለውጡ ዘመናት የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠልና የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ የሕዝብ ድጋፍ ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ የክልሉ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.