Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጋቢት ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎችን የሚያወሳ ሕዝባዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ከተሞች የመጋቢት ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎችን የሚያወሳ ሕዝባዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ፡፡

ከክልል እስከ ከተማ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን ጨምሮ የየከተሞቹ ነዋሪዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎቹ ተሳትፈዋል፡፡

በዚሁ ወቅት በክልሉ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎች ለማስቀጠል ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ መገለጹን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማጠናከር ሁሉም በየተሰማራበት መስክ ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ሥራዎችን መሥራት እንደሚጠበቅበትም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.