Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ለውጡን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ፤ “ትላንት፣ ዛሬ፣ እና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው የብዙኃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እመርታዊ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ማለታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው፤ የአሁኑ ትውልድ ሀገሩን ከተረጅነት በማላቀቅ እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷን በማረጋገጥ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለበት ብለዋል።

መንግሥት ለስፖርቱ በሰጠው ትኩረት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከ1 ሺህ 300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያዎች መገንባታቸውን የገለጹት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.