Fana: At a Speed of Life!

የኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሲደረጉ ፉልሀም ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ብራይተን ከኖቲንግሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ቀን 9 ሰዓት ከ15 ላይ በማርኮ ሲልቫ የሚመራው ፉልሀም በሜዳው ክራቨን ኮቴጅ ክሪስታል ፓላስን ያስተናግዳል፡፡

ፉልሀም በጥሎ ማለፉ በዚህ የውድድር ዘመን በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ማንቼስተር ዩናይትድን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

በኦሊቨር ግላስነር የሚመራው ክሪስታል ፓላስ በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት አላስተናገደም፡፡

ባለሜዳው ፉልሀም በበኩሉ በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ድል የቀናው በሁለቱ ብቻ ነው፡፡

በሌላ ጨዋታ ብራይተን በሜዳው ኖቲንግሀም ፎረስትን ምሽት 2 ሰዓት ከ15 ላይ ያስተናግዳል፡፡

ብራይተን በጥሎ ማለፉ ኒውካስል ዩናይትድን በመርታት ሩብ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ኖቲንግሃም ፎረስት ደግሞ ኢፕስዊች ታውንን በመለያ ምት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.