Fana: At a Speed of Life!

በማይናማር የርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ትናንት በማይናማር በተከሰተው ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ ማለፉ ተነገረ።

ትንናት ሀገሪቱን ክፉኛ የመታትና በሬክታር ስኬል 7 ነጥብ 7 በተለካው ርዕደ መሬት በፍርስራሽ ስር በህይወት የተረፉን የመፈለጉ ስራ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።

የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው ማንዳላይ በርዕደ መሬቱ ክፉኛ የተመታች ሲሆን ከሟቾቹ አብዛኛውን ቁጥር የያዙት የዚህች ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ለርዕደ መሬቱ መነሻ ነጥብ የቀረበችው ከተማዋ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደች ሲሆን፤ በርካታ ህንጻዎቿ ወደ ፍርስራሽነት መለወጣቸው ተጠቅሷል።

ርዕደ መሬቱ የማይናማር ጎረቤት በሆነችው ታይላንድም ጉዳት አድርሶ በግንባታ ላይ የነበረ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ጭምር ተደርመሶ 6 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

በቴዎድሮስ ሳህለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.