Fana: At a Speed of Life!

ኢድ አልፈጥርን የተቸገሩትን በመደገፍ ማክበር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዘንድሮው የረመዷን ጾም ፍቅርና አብሮነትን የሚያሳዩ የጋራ የኢፍጣር መርሐ-ግብሮች የታዩበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ጨረቃ ዛሬ ማታ ከታየች ነገ፤ ጨረቃ ዛሬ ካልታየች ደግሞ ሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የዘንድሮው የኢድ አል ፈጥር በዓል ተከብሮ እንደሚውል ተመላክቷል።

በጀማል አሕመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.