Fana: At a Speed of Life!

ከ264 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከመጋቢት 12 እስከ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ ክትትል 264 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል 250 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የገቢ እና 13 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የወጪ ሸቀጥ እንደሆነ ተገልጿል።

የተለያዩ ማእድናት፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዛቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን፤ 16 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.