Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የኮሌራ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ከ990 ሺህ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርግ የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ክትባቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ የኮሌራ ወረርሽኝ በተከሰተባቸው ወረዳዎች ጊዜያዊ የኮሌራ ማከሚያ ማዕከላት ተቋቁመዋል፡፡

ለወረርሽኙ የተሰጠው ምላሽ ውጤታማ ይሆን ዘንድም፤ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማስተባበር ዘርፈ ብዙ የንቅናቄ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኮሌራ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆንመም ሁሉም የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ በበኩላቸው፤ በክልሉ ከየካቲት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የኮሌራ በሽታ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን አውስተዋል፡፡

ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ አግባብ በተከናወነው ሥራም የበሽታውን ስርጭት መቀነስ መቻሉን ጠቁመዋል።

ዛሬ የተጀመረው ክትባት በሽታውን ከመከላከልና የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ጎን ለጎን ዓይነተኛ መፍትሔ በመሆኑ፤ ሕብረተሰቡ በየአካባቢው የክትባት ማዕከል በመሄድ ክትባቱን እንዲወስድ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.