ሌሶ ኢትዮጵያ በመና አቡቹ ክፍለ ከተማ ያስገነባው ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የንፁህ መጠጥ ውሀ ማስተላለፊያ እና የኤሌክትሪክ ቱቦዎችን በማምረት ላይ የተሰማራው ሌሶ ኢትዮጵያ በሸገር ከተማ አስተዳደር በመና አቡቹ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን ፋብሪካ አስመርቋል።
ፋብሪካው ከ150 በላይ የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።
ሌሶ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም እነዚህን ምርቶች ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ብቸኛ ወኪል የነበረ ሲሆን፤ እንደ ሀገር ያለውን የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለማስቀረት በማሰብ ፋብሪካ ማቋቋሙ ተጠቁሟል።
ድርጅቱ ዛሬ ከሚያስመርቀው የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በተጨማሪ የሁለተኛው ምዕራፍ የፋብሪካ ግንባታን ያስጀምራል።
ሌሶ ኢትዮጵያ የቻይና ሌሶ ግሩፕ አካል ሲሆን ግሩፑ በተለያየ የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ የተሰማራ ነው።
በዛሬው እለት በተመረቀው ፋብሪካ የሚመረቱ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የቱቦ ምርቶች አለም አቀፍ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ተብሏል።