የዒድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ ቦታን የማፅዳት መርሐ-ግብር ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ሐይማኖቶች አባቶች እና ተከታዮች 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የሚከበርበትን ቦታ አጽድተዋል።
በበልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሐረር የሰላም፣ የፍቅርና የመቻቻል ዕሴት በተግባር የሚታይበት ከተማ ናት፡፡
ይህም በሕዝቦችና በሐይማኖቶች መካከል አብሮነትና መቻቻልን በማጎልበት ረገድ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የጽዳት መርሐ-ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ በክልሉ መሰል የመደጋገፍ ዕሴቶች በሐይማኖቶች መካከል መቻቻል፤ አብሮነትንና ሰላምን እያጎለበቱ ነው ብለዋል።