Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አስትሮኖሚካል ማህበር ጉባኤን እንድታዘጋጅ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ 8ኛውን የአፍሪካ አስትሮኖሚካል ማህበር ጉባኤ አዘጋጅ ሀገር ሆና መመረጧን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ የአፍሪካ አስትሮኖሚካል ማህበር ኮንፍረንስና ጠቅላላ ጉባኤን ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ ባደረገው ውድድር ነው ኢትዮጵያ የተመረጠችው።

በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ከመጋቢት 15 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው 5ኛው የአፍሪካ አስትሮኖሚካል ማህበር ኮንፍረንስና ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ኢትዮጵያዊው አማረ አበበ (ፕ/ር) ተመርጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.