ክሪስታል ፓላስ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀን 9 ሠዓት ከ 15 ላይ በክራቨን ኮቴጅ በተደረገ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ፉልሀምን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የክሪስታል ፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ኢዜ እና ሳር በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥሩ፤ ተቀይሮ የገባው ኤዲ ኒኪታህ ቀሪዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡
በዛሬው ጨዋታ ድል የቀናው ክሪስታል ፓላስ በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡
የኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ሲቀጥል ብራይተን በሜዳው ኖቲንግሀም ፎረስትን ምሽት 2 ሠዓት ከ 15 ላይ ያስተናግዳል፡፡