ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ቅዳሜ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የዘንድሮው የረመዷን ጾም ፍቅርና አብሮነትን የሚያሳዩ የጋራ የኢፍጣር መርሐ-ግብሮች የታዩበት እንደነበረም ገልጸዋል።