Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ምክንያት የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ፡፡

የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

በዚህም መሠረት፤
👉 ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ በተመሳሳይ ከቦሌ አካባቢ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፤

👉 ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፤

👉 ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች፤

👉 ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ -ሳንጆሴፍ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፤

👉 ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ቡልጋሪያ መብራት ላይ፤

👉 ከቅድስት ልደታ ፀበል በAU ቅዱስ ሚካኤል መታጠፊያ ወደ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ፤

👉 ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አደባባይ ላይ፤

👉 ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት ፈረሰኛ መብራት ላይ፤

👉 ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ፤

👉 ከመርካቶ አካባቢ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ፤

👉 ከፒያሳ በባንኮዲሮማ መብራት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮዲሮማ መብራት ላይ፤

👉 ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ሴቶች አደባባይ ላይ ከንጋቱ 11 ሠዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

ሕብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.