አቶ አደም ፋራህ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አደም ፋራህ በመልዕክታቸው፤ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።