የዒድ አልፈጥር በዓል አንድነት የሚጠናከርበት እንዲሆን እመኛለሁ- ከንቲባ አዳነች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢድ አልፈጥር በዓል የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና አንድነት የሚጠናከርበት እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ ለ1 ሺህ 446ኛው ዒድ አልፈጥር በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፤ መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ ብለዋል፡፡
የዒድ አልፈጥር በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና በረመዳን የጾም ወር የነበረው መተሳሰብ፣ መረዳዳት እና አንድነት የሚጠናከርበት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ሲሉ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡