የዒድ አልፈጥር በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በማሰብ ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዒድ አልፈጥር በዓል ሲከበር የተቸገሩና አቅመ ደካማ ወገኖችን በማሰብ መሆን እንዳለበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስገነዘበ፡፡
ምክር ቤቱ የዒድ አል-ፈጥር በዓልን በማስመልከት ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፏል።
በመልዕክቱም፤ የረመዳን ወር ሕዝበ ሙስሊሙ ወደ ፈጣሪው ይበልጥ የሚቀርብበት የፆምና ፀሎት ወቅት መሆኑን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡
በዓሉ የሠላም የመረዳዳትና የመተሳሰብ እንዲሁም የተቸገሩና አቅመ ደካማ ወገኖችን የምናስብበት ሊሆን ይገባል ብሏል፡፡