Fana: At a Speed of Life!

ርዕሳነ መስተዳድሮች ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች 1 ሺህ 446ኛዉን የዒድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓሉ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተባበር መንፈስን ማደሻ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ በዓሉን ስናከብር ያለንን በማካፋል አቅመ ደካሞችን በመጠየቅና የተለመደውን እርስ በርስ የመረዳዳት ልምድ በማጎልበት መሆን አለበት ብለዋል።

በተመሳሳይ የሐረሪ ክልል መንግስት ለዒድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፤ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.