Fana: At a Speed of Life!

ርዕሳነ መስተዳድሮች ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ለሕዝበ ሙስሊሙ መልካም የኢድ አልፈጥር በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

በዓሉ አንድነታችንን የምናጠናክርበት፣ ድህነትን የምናሸንፍበት፣ አቅመ ደካሞችን የምንረዳበትና ከፈጣሪ በረከት የምናገኝበት ይንልን ሲሉም መልካም ምኞታቸቸውን ገልጸዋል፡፡

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል ዓርባ በበኩላቸው ዒድ በየአመቱ ደስታን ይዞ የሚመለስ አመታዊ ክስተት ነው፤በዓሉ የሰላም፣የጤናና የደስታ እንዲሆን ልባዊ መልካም ምኞቴን ለሙስሊሙ ማህበረሠብ በአክብሮት እገልጻለሁ ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት  በዓሉን ስናከብር ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፤ የመደጋገፍ እና የአንድነት እሴቶች በማጠናከር እንዲሆን አደራ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር አብሮነትንና መደጋገፍን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

በዓሉን ስናከብርም የመተሳሰብና የሰላም ዕሴቶቻንን ከሚያጎድፉ ተግባራት በመታቀብ የክልሉን ከፍታ እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ሚና በመወጣት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

ሕዝቡ ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፣ የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ ዕሴት በማጠናከር ሀገራዊ የለውጥ ጉዞውን እንዲያሳካም ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.