ብልጽግና ፓርቲ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፏል።
ፓርቲው በመልዕክቱ፤ በዓሉ የኢትዮጵያውያን ህብረት የሚደምቅበት፣ ሰላም የሚረጋገጥበት እና አንድነት የሚጠናከርበት እንዲሆን ተመኝቷል።
በተጨማሪም እርስ በርስ በመረዳዳት ለብልፅግና በትጋት የሚሰራበት እንዲሆን በመመኘት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቱን አስተላልፏል።