Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ውድ ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.