የዒድ አልፈጥር በዓል ተከበረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሯል።
የዒድ አልፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው የተከበረው።
በዓሉ በተለያዩ ከተሞች በድምቀት የተከበረ ሲሆን÷ሕዝበ ሙስሊሙ በማክበሪያ ሥፍራዎች በመገኘት የዒድ ሶላት ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።
በታላቁ የረመዳን ወር መጨረሻ የሚከበረውን የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም፣ በመተሳሰብና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።