በረመዳን ጾም ወቅት የነበረው መረዳዳትና መተሳሰብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በረመዳን ጾም ወቅት የነበረው መረዳዳት እና መተሳሰብ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አል ፈጥር በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በመልዕክቱም በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የረመዳን ወር ዘንድሮም በአማረና በደመቀ መልኩ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን አጠናክሮ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡
በዚህ መሠረት ዛሬ የዒድ አል ፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ ነው ያመላከተው፡፡
በጾሙ ወቅት የነበረው እዝነት፣ መተሳስብና መዓድ ማጋራት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ባህል ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡