የዒድ አል ፈጥር በዓልን በቸርነትና በእዝነት ማሳለፍ ይገባል – የፌዴሬሽን ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዒድ አል ፈጥር በዓልን በቸርነትና በእዝነት ማሳለፍ እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በመልዕክቱም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የረመዳንን የጾም ወቅት በመደጋገፍ እና መረዳዳት ማሳለፉን አውስቷል፡፡
የዒድ አል ፈጥር በዓልን በቸርነትና በእዝነት ማሳለፍ እንደሚገባ ያስገነዘበው ምክር ቤቱ÷በዓሉ የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡