Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ፌደራል ፖሊስ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለሃይማኖት አባቶች ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪም ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ለወጣቶች እንዲሁም ከበዓሉ ዋዜማ ጀምረው የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡ የጸጥታ ሃይሎች ምስጋና ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.