የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ለማድረግ በትኩረትና በትብብር መስራት ይገባል- ከንቲባ አዳነች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታለመው የኢትዮጵያ ከፍታ እና ብልጽግና እውን እንዲሆን በትኩረት እና በትብብር መስራት ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራ ላይ ለሚሳተፉ ወጣቶች ማዕድ አጋርተዋል፡፡
ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የታለመውን የኢትዮጵያ ከፍታ እና ብልጽግና ለማሳካት ያለማቋረጥ በትብብርና በትጋት እየተሰራ ነው፡፡
ለአብነትም በበዓላት ወቅት ጭምር ያለ እረፍት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ለዚህም ለከተማዋ ውበትና እድገት ወሳኝነት ባለው የኮሪደር ልማት ሥራ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ለማድረግ 24 ሰዓት መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ከንቲባዋ÷ ወጣቶች ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ እስክትበለጽግ ድረስ እረፍት የለንም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በታምራት ደለሊ