Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አድማ መከላከል አባላት የጎንደር አብያተ መንግሥታትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የ33ኛ ዙር የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላት የጎንደር አብያተ መንግሥታትን እና የከተማዋን የኮሪደር ልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል።

ጎብኚዎቹ በጎንደር ከተማ እና  በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተመደቡ የ3ኛ ሻለቃ የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የአድማ መከላከል አባላቱ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው፤  ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ዝግጁነታቸውን እንደገለጹ አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.