Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ሃይማኖት እኩልነትና መቻቻል መስፈኑን አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በለውጡ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትና መቻቻልን ማስፈን ተችሏል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፥ ሕዝበ ሙስሊሙ ለበርካታ ዘመናት ያነሳቸው የነበሩ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል አመራርነት መልስ አግኝተዋል።

ከዚህ ባለፈም በለውጡ መንግስት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በኢትዮጵያ የሃይማኖት ነፃነትና መቻቻልን ማስፈን ተችሏል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ከለውጡ በፊት ጥያቄዎችን የሚያነሱ የሃይማኖት መሪዎችና ተወካዮች በተለያዩ ማጎሪያዎች ይታሰሩ የነበረበትን ሁኔታ የለውጡ መንግስት ማስቀረቱን አንስተዋል፡፡

አቶ ሙስጠፌ በኢትዮጵያ የሃይማኖት እኩልነትና መቻቻልን እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በጾም ወቅት ሲያሳይ የነበረውን መልካም ተግባር በማስቀጠል የኢትዮጵያን ሰላምና ልማት በጋራ ማጠናከር እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.