የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 6ኛ ዙር የዲፕሎማቶች ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስድስተኛ ዙር ሰልጣኝ ዲፕሎማቶችን ስልጠና በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
በመርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ስልጠናው ለቀጣይ 4 ወራት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጥ ሲሆን÷ሰልጣኞች በቆይታቸው የፖሊሲ፣ የአካዳሚክና ተግባር ተኮር ስልጠናዎች እንደሚወስዱ ተገልጿል።