ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የወንጀል ምርመራ ቡድን በማቋቋም በትብብር ለመሥራት ተነጋገሩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮለኔል አብደላ መሃመድ ጋር በወንጀል ምርመራ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በዱባይ ወንጀል ሠርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተከናወነ ነው።
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮለኔል አብደላ መሃመድ በበኩላቸው፤ በቀጣይ ለሚከናወኑ የጋራ የወንጀል ምርመራ ሥራዎች ወደ ዱባይ የሚሄዱትን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኃላፊዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት ተፈላጊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የወንጀል ምርመራ ቡድን በማቋቋም በትብብር እንደሚሠራ ሁለቱ ወገኖች መክረዋል፡፡