Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ምቹ የትምህርት ምህዳር መፍጠር ይገባል – ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ምቹ የትምህርት ምህዳር መፍጠር ወሳኝ ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሯ በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በጆር ወረዳ የተገነባውን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ህንጻ እና የመንገድ ዳር የገበያ ሼድ መርቀዋል።

ወ/ሮ አለሚቱ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ምቹ የትምህርት አካባቢን መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡

የት/ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና ተፈላጊውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በክልሉ በት/ቤቶች የሚስተዋሉ እጥረቶች ለመፍታትና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ላደረገው ድጋፍ ርዕሰ መስተዳድሯ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የተገነባው የመንገድ ዳር መገበያያ ሼድ የሕብረተሰቡን የገበያ ትስስር ከማሳደግ ባለፈ ምቹ የገበያ ሁኔታን ይፈጥራል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.