ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ዕጩ መልማይ ኮሚቴን ሰየሙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ዕጩ መልማይ ኮሚቴን ሰየሙ፡፡
ኮሚቴው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 133/2011 አንቀጽ 5(1) መሠረት ነው ከመጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተሰየመው፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
1. ቀሲስ ታጋይ ታደለ – ሰብሳቢ
2. ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ – አባል
3. አቶ ባዬ በዛብህ – አባል
4. ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ – አባል
5. አቶ ካሳሁን ፎሎ – አባል
6. ወ/ሮ እርግበ ገ/ሐዋሪያት – አባል
7. ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ – አባል
8. ሰብስብ አባፍራ አባጆብር – አባል