Fana: At a Speed of Life!

24 የተሽከርካሪ ዓመታዊ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 24 የተሽከርካሪ ዓመታዊ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ ርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ተቋማትን በመገምገም ነው የጎላ ክፍተት የተገኘባቸው 24 ተቋማት ላይ ርምጃ የወሰደው፡፡

በዚህ መሰረትም 2 የምርመራ ተቋማት ፈቃዳቸው የተሰረዘ ሲሆን÷ 4 ተቋማት ደግሞ ለሶስት ወራት ታግደው ክፍተታቸውን እንዲያርሙ ተወስኗል፡፡

በተጨማሪም 6 ተቋማት ለአንድ ወር ሥራ እንዲያቆሙ እንዲሁም 12 ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በቁርጠኝት እንደሚሰራም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.