የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ውጥንን መነሻ ያደረገ ኢኒሼቲቭ ነው – አቶ አረጋ ከበደ
የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ውጥንን መነሻ ያደረገ ኢኒሼቲቭ ነው – አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ውጥንን መነሻ ያደረገ የብልጽግና ፓርቲ ኢኒሼቲቭ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንዳሉት÷የሌማት ትሩፋት የእንስሳት ሃብት ምርቶች የቅንጦት ምርቶች ሳይሆኑ ሕዝቡ በቀላሉ እያመረታቸው በሌማቱ ላይ እንዲያገኛቸው የሚያደርግ የመጋቢት 24 በረከት የሆነ የብልጽግና ፓርቲ ኢኒሼቲቭ ነው።
የሌማት ትሩፋት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማላቅ ያለመ የብልጽግና ፓርቲ እሳቤ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የምግብና የሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ውጥንን መነሻ ያደረገ ከመጋቢት 24 በረከቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ለዚህም በረከተ ብዙ በሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የብልጽግና ፓርቲ እሳቤና ተግባራዊ የሌማት ትሩፋቶች ማሳያዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።