Fana: At a Speed of Life!

100 በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የብዙኃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ 100 አውቶቡሶችን ሥራ አስጀመረ፡፡

አውቶብሶቹ የቅድመ ክፍያ ካርድን ጨምሮ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥን መያዛቸው ተገልጿል፡፡

በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች ስምሪት ወስደው እንደሚሠሩም ተመላክቷል፡፡

በአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና ሌሎች የከተማዋ እና የፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሚኪያስ ዓለሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.