የዓለም አቀፍ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፍ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሪናሬ ዋታናቤ አዲስ አበባ ገቡ።
የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ገበያው ታከለ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸል።
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከባህልና ስፖርት ሚኒስትሮች ጋር እንደሚወያዩና የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ስፖርት ያለበትን ደረጃ እንደሚገመግሙ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡