Fana: At a Speed of Life!

የለውጡ ፍሬ የሆኑ ግዙፍ ልማቶች የህዝቡን የኑሮ ደረጃ እያሻሻሉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ከመጋቢት እስከ መጋቢት’ በተደረገው ቅንጅታዊ ርብርብ በየአካባቢው የተገነቡ ግዙፍ ልማቶች የህዝቡን የኑሮ ደረጃ እያሻሻሉ እንደሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

የመዲናዋንና የሀገሪቱን ገፅታ እየቀየሩ የሚገኙት ግዙፍ የልማት ስራዎች ከመጋቢት እስከ መጋቢት በተደረገው ቅንጅታዊ ርብርብ የተመዘገቡ የለውጡ ፍሬዎች መሆናቸውንም ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፀጥታ አካላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአዲስ አበባ የተገነቡ ግዙፍና ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው፡፡

ጉብኝቱ ለላቀ ድል ተጨማሪ ተነሳሽነትን ለመሰነቅ የሚያስችል መሆኑን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.