የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አመራሮችን ያሳተፈው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ “ትናንት፣ ዛሬንና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አመራሮች ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
በፍፃሜ ውድድሮቹም፤ በወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የተሠራው ሥራ በሀገራችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
በከተማ አሥተዳደሩ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ1 ሺህ 300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውንም አውስተዋል፡፡
በእነዚህ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም የተሳካ ስፖርታዊ ውድድሮች መከናወናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በሙባረክ ፋንታው