Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በጨረታው 12 ባንኮች መሳተፋቸውን ባንኩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስፍሯል፡፡

በዚህም አማካኝ የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር 131 ነጥብ 7095 ብር ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል።

የውጭ ምንዛሪ የገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ ያስታወቀው ባንኩ፤ ቀጣዩ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.