Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ልዩ መልዕክተኛ አማንዲፕ ሲንግ ጊል (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ አማንዲፕ ሲንግ ጊል (ዶ/ር)ተባበሩት መንግሥታት በዲጂታይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ባቋቋመው አዲስ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ አንድ አካል ሆና በንቃት እንድትሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲሱ የመንግሥታቱ የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ወጥ የሆነ አስተዳደር ለማውጣት እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለመሥራት የተቋቋመ እንደሆነም ተገልጿል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታይዜሽን አስፈላጊነት ለሀገር እድገት ሊጫወት የሚችለውን ቁልፍ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሰሩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንስቲትዩቱ እና መሰል ተቋማት አስቀድሞ እንዲቋቋሙ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት አዲሱ ኢኒሼቲቭ አካል መሆኗ ቁልፍ ተግባር እንደሆነና በንቃት እንደምትሳተፍ ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.