በሻሸመኔ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 7ኛ ዓመት አስመልክቶ በሻሸመኔ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
በሰልፉ ላይ ከምዕራብ አርሲ ዞን 13 ወረዳዎች፣ 2 ከተማ አስተዳደሮች እና ከሻሸመኔ ከተማ 4 ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን፤ የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተውበታል።
ሰልፈኞቹ በለውጡ መንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ባስተላለፉት መልዕክት አረጋግጠዋል።
በጌታቸዉ ሙለታ