በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የለውጡን 7ኛ ዓመት አስመልክቶ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመጋቢት ፍሬዎችና የቀጣይ የኢትዮጵያ ተስፋዎች ዙሪያ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
“ትናንት ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘው መድረኩ፤ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የተበሰረበት እና ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበት ወቅት በመሆኑ መጋቢት 24 ልዩ ወር መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በመድረኩ ላይ፤ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማስረሻ በላቸው፣ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥ ሥራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በየሻምበል ምኅረት