ለውጡ እውን የሆነበት 7ኛ ዓመት የድጋፍ ሰልፍ በአሶሳ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የተደረገውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የተገኙ ትሩፋቶችን የሚዘክር የድጋፍ ሠልፍ እየተካሄደ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ “መጋቢት 24 የቀጣዩ አርበኝነት ጅማሮ ማብሰሪያ ነው፣ የጋራ ግባችን የአፍሪካ ተምሳሌትነት ነው፣ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን ለአዎንታዊ ሰላማችን፣ የመጋቢት 24 ድልን በኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እንደግመዋለን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በሕዝባዊ ድጋፍ ሰልፉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአሶሳ ከተማ እና የአሶሳ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።