Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎች ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የፓናል ውይይቶች እየተካሄዱ ነው፡፡

በሐረሪ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚዳስስ የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎች በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሐረሪ ጉባዔ አፈ-ጉባዔ ሙህየዲን አሕመድ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ሮዛ ኡመር፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ክላስተር “መጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎች ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል መሪ ሐሳብ የለውጡ መንግሥት 7ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር)፣ የዲላ ክላስተር ቢሮ ኃላፊዎች፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴን (ዶ/ር) ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተለያየ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ከተወለደበት በሰባት ዓመት ጉዞ ውስጥ በሁሉም ዘርፎች በተመዘገበው ለውጥ ዙሪያ ሠነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ የጌዴኦ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ በድሬዳዋ አሥተዳደር ”የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል በሪ ሐሳብ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ መሆኑን የአሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በሲዳማ ክልል የለውጡን 7ኛ ዓመት አስመልክቶ በተዘጋጀ ሠነድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በዚሁ ወቅትም፤ የለውጡ መንግስት ኅብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት ያለውን ሀብት በመጠቀም እና በመደመር እሳቤ በተለያዩ ምኅዳሮች ሁሉም እኩል የሚሳተፍበት ሂደት ማረጋገጡ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.