በአማራ ክልል ያሉ ጥያቄዎች ወደ ምክክር እንዲመጡ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ሰላም፣ ልማት እንዲሁም የሕዝቦች እኩልነትና ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማሟላት በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ጥያቄዎች ወደ ምክክር እንዲመጡ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከመጋቢት 27 ጀምሮ ለሚያካሂደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ተቋማቸው አካታችነትን እና የላቀ የማኅበረሰብ ተሳትፎ በማረጋገጥ የምክክሩን ግብ ለማሳካት በክልሉ ከመጋቢት 27 ጀምሮ ለ7 ቀናት የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ይሠራል።
የሀገርን ሰላም፣ ልማት እንዲሁም የሕዝቦችን እኩልነትና ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማሟላት፤ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የትኛውም ዓይነት ጥያቄዎች ወደ ምክክሩ እንዲመጡ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቅቋል ብለዋል፡፡
“ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የልሂቃን ሚና ምን መምሰል አለበት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
በደሳለኝ ቢራራ