Fana: At a Speed of Life!

ለውጡን ተከትሎ የተገኙ ውጤቶች የቤተሰብ ብልጽግናን በማረጋገጥ ሂደት ከፍተኛ ሚና አላቸው – አቶ አወሉ አብዲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ዕውን የሆነውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የተገኙት ውጤቶች የቤተሰብ ብልጽግናን በማረጋገጥ ሂደት ከፍተኛ ሚና አላቸው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ተናገሩ።

‘ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!’ በሚል መሪ ሐሳብ በአምቦ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፉ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ የምዕራብ ሸዋ ዞን ማህበረሰብ የተሳተፈ ሲሆን፤ የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በወቅቱ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ አወሉ አብዲ፤ የለውጡ እውን መሆን ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

የመጋቢት 24 ድል የረጅም ዘመናት የመስዋዕትነት እና የትግል ውጤት ነው ብለዋል፡፡

ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተገኙት የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውጤቶች የቤተሰብ ብልጽግናን በማረጋገጥ ሂደት ከፍተኛ ሚና አላቸው ማለታቸውን የምዕራብ ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.